“ተመስገን ሕመሙ ፀንቶበታል” የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

በዝዋይ ማረሚያ ቤት የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሕመሙ ፀንቶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር የገለፁት ቤተሰቦቹ፤ የማረሚያ ቤት ባለሥልጣናት የጤንነት ሁኔታውን አስመልክቶ መረጃ እንደከለከሏቸው ቤተሰቦቹ አስታወቁ።

በስም ማጥፋት፣ ሕዝብን በማነሳሳትና ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ክስ የሦስት ዓመት እስራት የተፈረደበትን ጋዜጠኛ እስራት የመብት ድርጅቶች ሲያወግዙና ጋዜጠኛው እንዲፈታ ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል።

ተመስገን ከዚህ ቀደም በእስር ላይ የሕክምና አገልግሎት ተከልክሎ እንደነበር የጋዜጠኛ ተሟጋች ቡድኑ/CPJ/ በተደጋጋሚ መዝግቧል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

“ተመስገን ሕመሙ ፀንቶበታል” የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች