ጅማ ዩኒቨርስቲ ለመረጋጋት እየሰራ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተውን የተማሪዎች ሞት ተከትሎ በጅማ ዩኒቨርስቲ የሌሎች ክልል ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው እንዳይወጡ ጥረት ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ:: በቤተክርስቲያንና መስጊድ ተጠልለው የሚገኙ ተማሪዎችንም ለመመለስ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ተናግረዋል::