በኢትዮጵያ ታስረው ከቆዩ የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ሶስቱ ዛሬ ተፈቱ

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

ዞን ዘጠኝ

በአጠቃላይ 5ቱ እንዲፈቱ መወሰኑን ፋና ዘግቧል፤ በሌሎቹ ላይ ክሱ ይቀጥላል ብሏል።

በኢትዮጵያ ከ1ዓመት በላይ ታስረው ከቆዩ ጋዜጠኞችና የዞን ዘጠኝ ጦማር ጸሀፊዎች መካከል፤ ሶስቱ መፈታታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከምንጮቹ አረጋግጧል፤ የፋና ሬድዮ የተፈቱት ጋዜጠኞችና የጦማር ጸሃፊዎች 5 ናቸው ሲል ዘግቧል።

በሽብር ወንጀል ተከሰው ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር በእስር ያሳለፉት ጋዜጠኞቹ ተስፋለም ወልደየስና አስምማው ሃይለ-ጊዮርጊስ እንዲሁም የዞን 9 ጦማር ጸሃፊና የህግ መምህር ዘላልም ክብረት ዛሬ ማምሻውን ከእስር ተፈተዋል።

ከጦማር ጸህፊዎቹና ጋዜጠኞቹ ስምንቱን የሚወክሉት ጠበቃ አምሃ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ በተለይ እንደገለጹት፤ ሁለቱ ሴቶች ማለትም ኤዶም ካሳየና ማህሌት ፋንታሁን ከእስር ቤት ማምሻውን አልተለቀቁም።

ሔኖክ ሰማእግዜር ማምሻውን አነጋግሯቸዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ታስረው ከቆዩ የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ሶስቱ ዛሬ ተፈቱ