በእስራኤል የታጋቾቹን መገደል ተከትሎ የሥራ ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ

Your browser doesn’t support HTML5

የስድስት እስራኤላዊያን ታጋቾች አስከሬኖች በደቡባዊ ጋዛ በሚገኝ በምድር ውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ ዋሻ መገኘታቸውን ተከትሎ እስራኤላዊያን ድንጋጤ እና ቁጣቸውን መግለጻቸውን ቀጥለዋል። አንዳንዶቹም የሀገሪቱን መንግሥት ከሐማስ ጋር ቀደም ብሎ ከሐማስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለመቻል ወንጅለዋል።

ዛሬ ሰኞ በትልቁ የእስራኤል የሠራተኛ ማሕበር የተጠራ አገር አቀፍ የሥራ ማቆም አድማ ተካሂዷል።

ሊንዳ ግራድስቲን ከእየሩሳሌም ያስተላለፈችው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።