ኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች በእምነት መሪዎች ላይ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት

ኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች በእምነት መሪዎች ላይ እየደረሰ ነው ያለው ጥቃት እንደሚያሳስበው በመግለፅ መንግሥት አጣርቶ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አመራር ቦርድ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

በሌላ በኩል “የሥራ አመራር ቦርድ ፅህፈት ቤቱ ያወጣው መግለጫ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ከሚመራው የኡለማዎች ምክር ቤት ዕውቅና ውጪ ነው” ሲል የኡለማዎቹ ምክር ቤት ተቃውሟል። “ቦርዱ እንዲህ ዓይነት መግለጫ የማውጣት ሥልጣንም የለውም” ብሏል ምክር ቤቱ አክሎ።

የኦሮምያ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ ሀሳሳ ላይ የተፈጠረው ስህተት መሆኑን መገምገሙን እና በሌሎች አካባቢዎች የተከናወነው ግን ሕግን የማስከበር ሥራ እንደሆነ ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች በእምነት መሪዎች ላይ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት