የሰሜናዊ ትግራይ አካባቢዎች በሰብአዊ ርዳታ መታጎል እየተቸገሩ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ድንበር አንዳንድ አካባቢዎች፣ በተለይም ለኢሮብ ወረዳ ሕዝብ፣ ዛሬም ሰብዓዊ ርዳታ እየደረሰ እንዳልኾነ፣ አንድ የአካባቢው ተወላጅ ለቪኦኤ ገለጹ፡፡ የዚኽም ምክንያት፣ ወደ ወረዳው የሚገባው መንገድ በመዘጋቱ እና በየትኛውም ወገን ትኩረት በመነፈጉ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡

የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፣ መንገዱን የኤርትራ ሠራዊት ኬላ ስለዘረጋበት የሰብአዊ ርዳታ ለማቅረብ እንደተቸገረ አስታወቀ፡፡

የኤርትራ መንግሥት፣ ከዚኽ ቀደም የሚቀርብበትን የትኛውንም ክሥ አልተቀበለም። የኢሮብ ወረዳን ሕዝብ በተመለከተም፣ እስከ አሁን የሰጠው ምላሽ የለም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።