ኢራን የመካከለኛ ርቀት ሚሳይል ሙከራ በመተኮስ፣ በፋርስ ባሕረ-ሰላጤ ያለውን ውጥረት ማባባሷን፣ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለሥልጣን አስታወቁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በስም እንዲጠቀሱ ያልፈለጉት እኝህ ወታደራዊ ባለሥልጣን ትናንት ሐሙስ እንደገለጹት፣ የዕሮብ ዕለታው የኢራን ሚሳይል ሙከራ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ወታደራዊ ጦር ሰፈር የሚያሰጋ አልነበረም።
ከደቡባዊ ኢራን ወደብ አካባቢ የተተኮሰው ሚሳይል፣ በ1,100 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ፣ በዋና ከተማዋ ምሥራቃዊ ቴህራን ላይ መውደቁም ተሰምቷል።
ሚሳይሉ ከመተኮሶ አስቀድሞ ግን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የኢራንን የሚሳይል ሙከራ ጣቢያ ስትከተል እንደነበር እኝሁ በስም ያልተጠቀሱ ወታደራዊ ባለሥልጣን ተናግረዋል።