ከዱራሜ እስከ ዋሽንግተን - የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ሴት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሎዛ አበራ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ እግርኳስ ቡድን አምበል ሎዛ አበራ ባለፈው ሳምንት የእግርኳስ ተጫዋችነት ፊርማዋን በዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው ዲሲ ፓወር ኤፊሲ አኑራለች፡፡


ለሁለት አመት የሚቆየው ይህ ኮንትራትም ሎዛ አበራን በሰሜን አሜሪካ የመጀመርያዋ ኢትዮጵያዊ የፕሮፌሽናል ተጫዋች አድርጓታል፡፡ አስማማው አየነው የአሜሪካ ድምጽ ስቱዲዮ ጋብዞ አነጋግሯታል፡፡