ሴቶች ከአመራርና ጠንካራ ዘገባዎች የተገለሉበት ጋዜጠኝነት

Your browser doesn’t support HTML5

የዛሬው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) 'ፍትሃዊነት' በሚል መሪ ቃል ስለ ዕኩልነት ብቻ ማውራት በቂ አይበቃም” በሚል በዓለም ዙሪያ እየታሰበ ነው። ሴቶችን በፍትሃዊነት ካለምንም አድልዎ ማብቃትና ወደፊት ማምጣት አስፈላጊ መሆኑንም ያሳስባል።

በኢትዮጵያ ሴቶች ዕኩል ተወዳዳሪ ካልሆኑባቸው ዘርፎች መካከል የብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን አንዱ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና የተግባቦት ት/ቤት መምህር በሆኑት በዶክተር ሙላቱ አለማየሁ እና በመብቶች እና የዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል /ካርድ/ በቅርቡ የተሠራ አንድ ጥናት አመላክቷል። እስካሁን በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን ዘርፉ የሚሠሩ ሴት ጋዜጠኞች ቁጥር ከጠቅላላው 25 ከመቶ ብቻ መሆኑን እና እነዚህ ሴቶች የዓመታት ልምድ ያካበቱም ቢሆኑ ወደ አመራር ደረጃ ከፍ አለማለታቸውን ጥናቱ ይጠቁማል።

ጥናቱን ያካሄዱት ዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ እና ሁለት ሴት ጋዜጠኞች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።