ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮን ለማገዝ የሚያስገድደውን የካምፓላ ስምምነት ፈረመች

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ምላሽ እቅድ ሪፖርት መሰረት ወደ 1.8 ሚሊየን የሚጠጉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሉ፡፡ኢትዮጵያ ከሰሞኑ እነዚህን ተፈናቃዮች የተመለከተ የካምፓላ ስምምነት በመባል የሚታወቅ አህጉራዊ ውል ፈርማለች፡፡ ስለ ውሉ ምንነት እና ስላለው ፋይዳ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል ፟አቀባይ የሆኑት አቶ ክሱት ገብረ እግዚአብሔር ለአሜሪካን ድምጽ አስረድተዋል፡፡