የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው ቦታዎች በተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተዘገበ

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አካል በሆነውና የህወሓት ኃይሎች ከዘጠኝ ወራት ቆይተውበታል በተባለው የዝቋላ ወረዳ እንዲሁም ለሦስተኛ ጊዜ በተቀሰቀሰው ጦርነት የጥቃት ኢላማ ነበሩ በተባሉት የሰቆጣ ወረዳና ዙሪያዎቹ አካባቢዎች የሚገኙ ከ26 በላይ የትምህርትና የጤና ተቋማት ውድመትና ዘረፋ ተፈጽመውባቸዋል ሲሉ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ትምህርትና ጤና መምሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡

በክልል ደረጃ መስከረም 9 አዲሱ የትምህርተ ዘመን የሚጀመርበት ቢሆንም ጉዳት በደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ላይ መርኃ ግብሩን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚቸገር ትምህርት መምሪያው ገልጿል፡፡