በዩናይትድ ስቴትስ የዋጋ ግሽበቱ አሳሳቢ ሆኗል

Your browser doesn’t support HTML5

በዓለም ላይ ብዙ አገሮች የዋጋ ግሽበት ወይም ኢንፍሌሽንን እየታገሉ ነው፡፡ ለዋጋ ግሽበቱ መነሻ የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የተለያዩ ምክንያቶች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡
በባይደን አስተዳደር ባላፈው ዓመት መጋቢት ወር ውስጥ በኮቪድ-19 ወረርሽኙ የተጠቁትን የአሜሪካ የንግድ ተቋማትና አሜሪካውያንን ለመደገፍ ወጭ እንዲሆን ያደረጉት የ1.9 ትሪሊየን ዶላር የኮቪድ-19 እፎይታ ገንዘብ የንግድ ተቋማትና አሜሪካውያን ቤተሰቦችንን ረድቷል፡፡
ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የዋጋ ግሽበት በምጣኔ ኃብቱ ላይ ትልቅ ችግር ደቅኗል፡፡