ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ እና የኢትዮጵያ መንግስት የአራት-ዓመት 3.4 ቢሊዮን ዶላር የብድር ዝግጅት የመጀመሪያ ግምገማ ለማጠናቀቅ በሚያስችሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን እቋሙ ባለፈው አርብ አስታውቋል፡፡
ግምገማው ሲጠናቀቅ "ኢትዮጵያ ወደ 345 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ እንድታገኝ ያደርጋታል" ሲልም አይ ኤም ኤፍ ገልጿል።
የብርን የመግዛት አቅም ካዳከመው የኢኮኖሚ ማሻሽያ ሁለት ወር በኋላ በተሰጠው የገንዘብ ተቋሙ መግለጫ '' የማሻሽያ ትግበራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው” ሲልም ገልጿል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የፋይናንስና ምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር አብዱል መናን ሙሃመድ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከማሻሽያው በኋላ ያለበት ሁኔታን ለመገምገም ጊዜው ገና ነው ይላሉ፡፡