ኢጋድ ስለደቡብ ሱዳን እየተነጋገረ ነው

  • እስክንድር ፍሬው
የኢጋድ አባላትና የሌሎችም አገሮች መሪዎች ለደቡብ ሱዳን ችግር እልባት በአዲስ አበባ ስብሰባ

የኢጋድ አባላትና የሌሎችም አገሮች መሪዎች ለደቡብ ሱዳን ችግር እልባት በአዲስ አበባ ስብሰባ

የኢጋድ አባላትና የሌሎችም አገሮች መሪዎች ለደቡብ ሱዳን ችግር እልባት ለመስጠት በአዲስ አበባ ስብሰባ በማካሄድ ላይ ናቸው።

የአማፅያኑ መሪ የሪያክ ማቻር ተወካዮች አገራቱ ጣልቃ ገብ ጦር እንዲልኩ ጥሪ እያቀረቡ ነው። የሪያክ ማቻር ቀኝ እጅና ዋነኛ ተደራዳሪ የነበሩት ጀነራል ታባይ ዴን ጋይ የሽግግር መንግስቱን ወክለው መገኘታቸው የስብሰባው መነጋገሪያ እንደሚሆን ተገምቷል።

የኢጋድ አባላትና የሌሎች አገራት መሪዎች በአዲስ አበባ የተሰባሰቡት የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት ይበልጥ በተወሳሰበበት ወቅት ነው።በብሔራዊ አንድነት የሽግግር መንግሥት ሲመሰርቱ ሁለት የነበሩት ዋንኛ ተቃናቃኞች አሁን ሦሥት ሆነዋል።ሁሉም የተጀመረው እአአ ሃምሌ 2008 ዓ.ም. በሽግግር መንግሥቱ ፕሬዝዳንቱ ሳልቫኬር ማያርዲት እና በአማፃንዩ መሪ ዶ/ር ሪያክ ማቻር መካከል ውግያ ሲከፈት ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኢጋድ ስለደቡብ ሱዳን እየተነጋገረ ነው