የአፍሪካ መሪዎች ያለመከሰስ መብት ጥያቄ

የአፍሪካ ኅብረት ካርታ እና ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት - ሄግ




አረንጓዴ - የሮማ ደንብን ስምምነት ፈርመው በፓርላማዎቻቸው ያፀደቁ፤ ቢጫ - የሮማን ደንብ የፈረሙ ግን በፓርላማዎቻቸው ያላፀደቁ፤ ቀይ - የሮማን ደንብ ያልፈረሙና የአይሲሲ አባል ያልሆኑ



Your browser doesn’t support HTML5

አፍሪካ ከአይሲሲ ጋር ያላት ግንኙነት




ሥራ ላይ ያሉ የሃገሮች መሪዎች እንዳይከሰሱ የሚያደርግ ከለላ ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ እንዲሰጣቸውና በኬንያ መሪዎች ላይ የተከፈተው ክስም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘገይ እንዲደረግም የአፍሪካ ሕብረት ሰሞኑን ጠይቋል፡፡

መሪዎቹ ባለፈው ቅዳሜ፣ ጥቅምት 2/2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት ስብሰባ ጉዳዩን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚያቀርብና የሚከታተል ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም /ፎቶ ፋይል/

በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የመሪዎቹ ጥያቄ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር እና የሕግ ጠበቃው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም /አልማርያም/ ለቪኦኤ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡