ክፍት የስራ ማስታወቂያ “ጅብ መጋቢ የመንግስት ሰራተኞች”- በሐረር ከተማ ገበሬዎች ከብቶቻቸውን ጅብ እንዳይበላባቸው በመፍራት የጀመሩት ባህል ዛሬ የቱሪስት መስህብ ሆኗል

Your browser doesn’t support HTML5

በጥንታዊቷ ከተማ ሲመሻሽ ሙዳ ስጋ በቀጭን እንጨት አንጠልጥለው ጅቦችን በመጥራት የሚመግቡ ሰዎች የቱሪስቶችን ቀልብ ስበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ቱሪዝምን ለማበረታታት በመንግስት ሰራተኝነት ጅብ መጋቢዎችን ሊቀጥር ክፍት የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል። ጅብ መጋቢዎቹ ከመንግስት ካዝና ለጅቦች የሚቀለብ ስጋና የወር ደመወዝ ይቆረጥላቸዋል በመንግስቱ እቅድ መሰረት።