ሔሪኬን ማርያ በፖርቶሪኮ

Your browser doesn’t support HTML5

ሔሪኬን ማርያ “በእንቅርት ላይ፣ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ ዛሬ ፖርቶሪኮ ላይ ከባድ ዝናብ አውርዷል። ቀደም ሲል የመላ ደሴቲቱ የኤለክትሪክ መብራት በሔሪኬኑ ምክንያት ጠፍቷል። ብዙ ቦታዎችን በጎርፍ አጥለቅልቋል። ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ጠፍቷል። ዶሚኒካን ሪፖብሊክ ላይ ደግሞ የአውሎ ነፋሱ ኃይል የቀነሰ ቢሆንም ጉዳት ማድረሱ አልቀረም።