በኢትዮጵያ ተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት ተፈጸሙ የተባሉ የመብት ጥሰቶች የሚያጣራ አካል አሁንም አወዛጋቢ ሆኗል

  • እስክንድር ፍሬው

ፋይል

በተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ወቅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች መጣራት ያለባቸው ገለልተኛ በሆነ የአገር ውስጥ ወይም የውጭ አካል መሆኑን ተቃዋሚዎች እያሳሰቡ ነው።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ግን ገለልተኛ አይደለም ብለዋል።

ይህን አስተያየት የማይቀበለው የኢትዮጵያ መንግሥት የማጣራቱን ሥራ የሚያከናወነው በተግባር የተፈተሸው ይሀው ኮሚሽን መሆኑን አስታውቋል።

እንዲጣሩ ጥሪ የቀረበው የሰብአዊ መብት ጥሰት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ሲካሄዱ በቆዩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ወቅት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ናቸው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች የሚያጣራ አካል አሁንም አወዛጋቢ ሆኗል