ከደጃፋቸው ላይ የተቀበሩት ቤተሰቦች

Your browser doesn’t support HTML5

የህወሓት ታጣቂዎች ተቆጣጥረዋቸው ከነበሩት የአማራ ክልል ከተሞች አንዷ በሆነችው “ሐይቅ” ከተማ ከአንድ ቤት አባትና ልጅን ጨምሮ በጦርነቱ ውስጥ ምንም ተሳትፎ ያልነበራቸው አራት ሰዎች በውጊያ ወቅት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።
ከሟቾቹ ሦስቱ በአንድ ቀን የተገደሉ ሲሆን አስከሬናቸውም በአንድ ላይ በግቢው ውስጥ ተቀብሯል። አራተኛዋ ሟች ደግሞ ህይወቷ ያለፈው በቀጣዩ ቀን በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ መሆንና ለቀናት በከተማዋ ጦርነት መደረጉን ነዋሪዎቹ አሰረድተዋል።