በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሞት የተጠረጠሩ ተያዙ

Your browser doesn’t support HTML5

ሃዋሳ ዩኒቪርሲቲ ውስጥ በግል ፀብ ተነሣ በተባለ ሰበብ አንድ ተማሪ በስለት ተወግቶ መሞቱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። በሁከቱ የተጠረጠሩ አርባ አራት ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መማክርትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፅሕፈት ቤት የሰጧቸውን መግለጫዎች የተንተራሰው ዘገባ ይናገራል። የዩኒቨርሲቲው ሥራ አልተቋረጠም።