የቤተሰብ በጎ አድራጊ ማኅበር - በሀዋሳ

Your browser doesn’t support HTML5

ባልተፈለገ እርግዝና፥ በባህልና ባለባቸው የአካል ጉዳትና አዕምሮ ዕድገት ውስንነት ምክንያት በወላጆቻቸው የተጣሉና በማኅበረሰቡ የተገፉ 88 ህፃናትን ከተጣሉበት አንስቶ የሚያሳድግ አንድ የቤተሰብ በጎ አድራጊ ማኅበር መንግሥት ማድረግ የሚገባውን ድጋፍ ባለማድረጉ ሊበተን መሆኑን ማኅበሩ ለቪኦኤ ተናገረ። የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የከተማው አስተዳደር ድጋፍ እንደሚያደርግ ከቪኦኤ ጋር በነበራቸስው ቆይታ አረጋግጠዋል።