በሃዲያ ዞን ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ

Your browser doesn’t support HTML5

በሃዲያ ዞን የሶሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚቃወም ሰልፍ በወረዳው ከተማ ጊንብቾ ተደረገ። ሰልፈኞቹ አስተዳዳሪው የተነሳው ያለምንም ቅድመ ሁኔታና ያለግምገማ መሆኑ አደባባይ እንድንወጣ አስገድዶናል ሲሉ በስልክ ለቪኦኤ ተናግረዋል። ከትናንት ጅምሮ የሃዲያ ዞን መንግሥት ኃላፊዎችን አስተያየት ለማካተት የተደረገ ጥረት አለመሳካቱ ተጠቅሷል።