54ኛው የጉርጉራ ጎሣ ኡጋዝ ዚያድ ዳውድ ዑመር በዓለ ሲመት አከባበር - ድሬዳዋ

Your browser doesn’t support HTML5

በሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖችና በዋናነት በድሬዳዋ ዙሪያ እንዲሁም በምስራቅ ኦሮሚያ ተሠባጥረው የሚገኙት የጉርጉራ ጎሣዎች 54ኛውን ኡጋዛቸውን (የጎሣ መሪያቸውን) ሾመዋል:: በበዓለ ሲመቱ ላይ ለመሳተፍ ከሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራሊያና ቻይና በርካታ የጎሳው ተወላጆች ተገኝተዋል:: ከዘጠኙም የሶማሌ ክልል ዞኖች ከሶማሊላንድ፣ ከኬንያና ጂቡቲ በእንግድነት ተጋብዘው የመጡ ኡጋዞች ፣ ሱልጣኖችና ገራዶችም ነበሩ::