የማረቆ ብሔረሰብ አቤቱታ በሃዋሳ

Your browser doesn’t support HTML5

የደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ማረቆ ብሄረሰብ በልዩ ወረዳነት እንዲደራጅና “ያለአግባብ በቤተጉራጌ መስቃን ወረዳ ሥር የተካለሉ” ያሏቸው ዘጠኝ ቀበሌዎች ወደ ማረቆ ወረዳ እንዲገቡ አቅርበናል ያሉት ጥያቄ አለመመለሱን የዞኑ ተፈናቃዮች ሃዋሳ ሄደው ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

በሌላ በኩል በማኅበረሰቦቹ መከከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በእርቀ ሰላም መቋጨቱን የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰሎሞን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጠው የአደረጃጀት እና የወሰን ጥያቄዎችን ለመመለስ ክልሉ ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።