Your browser doesn’t support HTML5
የዩናይትድ ስቴትስ ሕገመንግሥት የነፃነት ቀንዲል ሆኖ ለሃገሮችና በሃገሮች ሁሉ እንደአርአያ ይነሣል፤ ይወደሣል፡፡
አሜሪካዊያኑም ከሕገመንግሥታቸው በላይ አንዳች ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ይገነዘባሉና ለሁሉም ችግሮቻቸው መፍትሔ፣ ለሁሉም ጥያቄዎቻቸው መልስ ከሕገመንግሥታቸው ይሻሉ፤ ያከብሩታል፤ ይወድዱትማል፡፡
በአውሮፓ አቆጣጠር ዲሴምበር 15 ቀን 1791 ዓ.ም የወጣው የሕገመንግሥቱ የመብቶች ድንጋጌ አሥር ማሻሻያዎች የሚጀምሩት መሠረታዊ በሆነው ሃሣብንና ዕምነትን የመያዝ ነፃነትና መብት ሲሆን ይህንን ነፃነት ሊጋፋ የሚችል አንዳችም ሕግ በሕግ አውጭው የተወካዮች ምክር ቤት እንዳይወጣም አንቀፁ አጥብቆ ይከለክላል፡፡ ሕጎች ሁሉ በአሜሪካ ሲወጡ እያንዳንዳቸው ከዚህ ነፃነት መከበር አኳያ ይፈተሻሉ፡፡
ይህንን አውራ ማሻሻያ ወዲያው ተከትሎ የሰፈረው የመብቶች ድንጋጌ ሁለተኛው ማሻሻያ ሰዎች መሣሪያ የማግኘትና የመያዝ መብት እንዳላቸው ያረጋግጣል፡፡
ፖሊስ ደርሶበት አዳም እራሱን ቀድሞ ባያጠፋ ኖሮ የበለጠ ሰው መፍጀት የማችል መሣሪያና ጥይት ይዞ እንደነበር ታውቋል፡፡
ይህ አጋጣሚ ወዲያው ንግግር ያደረጉትን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በአደባባይ አስለቅሷል፤ ብዙዎችን አስለቅሷል፡፡ ብዙዎች ውስጣቸው ደምቷል፤ ብዙዎች እስከዛሬም ያለቅሣሉ፡፡
ለሕገመንግሥቱ ሁለተኛ ማሻሻያ መከበር ቆምያለሁ የሚለውና ለወትሮው በብርቱ የሚሟገተው ከአራት ሚሊየን በላይ አባላት ያሉት “ብሔራዊ የነፍጥ ማኅበር” – National Rifle Association (NRA) አደጋው ከተፈጠረ ጀምሮ ድምፁን አጠፋፍቶ ቆይቶ ትናንት ማምሻውን መግለጫ ይዞ ወጥቷል፡፡ “… እንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ዳግመኛ እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚያስችል አስተዋፅዖ ለማበርከት ኤንአርኤ ዝግጁ ነው ብሏል፡፡ አስተዋፅዖው ምን እንደሚሆን ግን በዝርዝር አልተናገረም፡፡
‘መሣሪያ በመያዝና በባለቤትነት ነፃነት ላይ ገደብ ሊጣል ይገባል’ ለሚሉ ብዙ ተሟጋቾች የዓርቡ የኒው ታውን አጋጣሚ ነዳጅና አቅም የሰጣቸው ይመስላል፡፡ “ይህ አጋጣሚ አንዳች ተግባር ሣይፈፀምበት ቢያልፍ ለዋሽንግተን የሚቀራት ጠባሣ ይሆናል” ሲሉ ያስጠነቅቃሉ “ከቃላት ይልቅ ተግባር ተግባር ተግባር” እያሉ የሚጎተጉቱት፡፡
ኢትዮጵያን በተመለከተ እንዲህ ዓይነቱ የተናጠል የወንጀልና የጥፋት አድራጎት “ጠብመንጃ የያዘ፣ የተራበ ወታደር ዳቦ ሲለምን በታየባት ሃገር” ውስጥ ይፈፀማል የሚል ሃሣብ ለጊዜው እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡ በጦር መሣሪያ ባለቤትነት ላይ ግን ቁጥጥር መደረግ አለበት ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
“ነፃነትና ዴሞክራሲ የሌሎችን ሕይወት፣ ነፃነትና ዴሞክራሲ ማጥፋት አይደለም” የሚሉ በፅናት የተነሱ ዜጎቿ በቆሙባት አሜሪካ ይህ የኒው ታውን ትምህርት ቤት አጋጣሚ ለአዲስ የጦር መሣሪያ ባለቤትነት ቁጥጥር እርምጃ መንገድ ይከፍት ይሆን? ይህ ዛሬ አደባባይና ጠረጴዛ ላይ ያለ ጥያቄ ነው…
ዘገባውን ያዳምጡ፡፡