የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዙሪያ አስተያየት - ድሬዳዋ
Your browser doesn’t support HTML5
በትላንትናው እለት ይፋ የተደረገው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ላይ በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡበት ነው:: በድሬዳዋ ከተማም በግልና መንግሥት ትምህርት ቤቶች የተፈተኑ በርከት ያሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በውጤታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለማቅረብ ትላንትናና ዛሬ በትምህርት ቢሮ ተሰብስበው ነበር::