አዘዞ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው፤ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ አቅራቢያ “አዘዞ ቀበሮ ሜዳ” እየተባለ በሚጠራው መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ።

ቁጥራቸው ወደ 3 ሺሕ የሚጠጋው እነዚህ ተፈናቃዮች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ከሠሩላቸው መጠለያ ውጪ ድጋፍ ያደረገላቸው አካል አለመኖሩን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልናምግብ ዋስትና ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ሰሞኑን ለሕዝብ እንደራሲዎች ባቀረቡት ሪፖርት በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 1.4 ሚሊዮን ሰዎች መኖራቸውን ገልፀዋል። ተፈናቃዮቹም በቂ ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆነ ተናግረዋል።