ዩኮድ ገርል ሥልጠና ተጠናቀቀ

  • እስክንድር ፍሬው

ዩኮድ ገርል

በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ሀገር ቤት ካሉ በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር የተባበሩበት የሴት ተማሪዎች የኮምፒውተር ኮዲንግ ወይንም ቅመራ ሥልጠና ተጠናቋል፡፡

ዩኮድ ገርል የተሰኘ በአሜሪካ የሚገኝ ድርጅት በዚያው በተቋቋመው የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል ጋር በመተባበር ነው፤ ከ23 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ሥልጠናውን የሰጡት፡፡

በውጭ ሀገራት የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም በመሰል የቴክኖሎጂና የክህሎት ሽግግር ተግባራት እንዲሳተፉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሀገር ውስጥ ካሉት ጋር ከተቀናጁ የተለያዩ ክፍተቶችን መሙላት እንደሚችሉ ሥልጠናውን ያስረባበሩት ተናግረዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ዩኮድ ገርል ሥልጠና ተጠናቀቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ዩኮድ ገርል ሥልጠና ተጠናቀቀ