በጌዴኦ ዞን ሲቪሎች ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው አመለከቱ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ሲቪሎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ አመልክተዋል። የጌዴኦ ዞን አስተዳደር በበኩሉ ግለሰቦቹ በፌደራል የደህንነት እና ፀጥታ የጋራ ግብረሃይል በወንጀል ተጠርጥረው መያዛቸውን አረጋግጦ የታሰሩ ሰዎችን ቁጥር ግን ከመግለፅ ተቆጥቧል።

የ“ጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆነ ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን” የሚሉ ቡድኖች በህቡዕ ስለመደራጀታቸው መረጃ እንዳለው ያስታወቀው የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረሃይል፤ በዞኑ አመፅና ሁከት ለማስነሳት በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቦ ነበረ።