በጋምቤላ ያለው የጥሎሽ ባህል በወጣት የትዳር ጓዶች እና በሴቶች ላይ ያሳደረው ጫና

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር  በጋምቤላ ክልል በአኝዋ፣ በኑዌር፣ ማጃንግ እና በኦፖ ጎሳዎች ውስጥ “በሴቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶችን ለይቶ ለማውጣት ይረዳል” ያለውን ፈጣን የዳሰሳ ጥናት በቅርቡ ሰርቷል፡፡  በጋምቤላ ሴቶች እንደ ንብረት እንደ ሚቆጠሩ፣ በየዕለቱ በባሎቻቸው እንደሚገረፉ፣ ትዳር ለመመሥረት የሚሹ ወንዶች እህቶቻቸውን እንደጥሎሽ እንደሚለዋወጡና ሌሎችም በደልና ጫና የሚያሳድሩ ልማዶች እንዳሉ ጥናቱ ያሳያል፡፡