ወጣቶችና የመፈናቀል ጣጣው

ጋቢና ቪኦኤ የዘጋቢዎች መስኮት

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች ሰዎች ከቀያቸው፣ ከተወለዱበትና ጎጆአቸውን ቀልሰው ከሚኖሩበት ስፍራ ሲፈናቀሉ ኑሮአቸውም አብሮ ምስቅልቅሉ ይወጣል።

ቤተሰብ ይበተናል፣ ሕፃናት ትምሕርታቸው ያቋርጣሉ፣ ወጣቶች ከጀመሩት የሕይወት ጉዞ ይስተጓጎላሉ። በኢትዮጵያ በይፋ የተመዘገበ ቁጥር ባይኖርም በተለያየ ጊዜ ከተለያየ የአገሪቱ ክፍል ተፈናቅለው ከትምሕርታቸውና ከሥራቸው የመስተጓጎል ጣጣ የገጠማቸው ወጣቶች ቁጥር ብዙ ነው። መፈናቀል ወጣቶችን ምን አሳጣቸው? ለዛሬ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችን አነጋግረናል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)