በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና የወጣቶች ጭንቀት
Your browser doesn’t support HTML5
ከተጀመረ አንድ ዓመት የሞላው ጦርነት በሃገሪቱ ላይ ሰፊ የሆነ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ስነልቦናዊ ጫና እያሳደረ ይገኛል፡፡ ጦርነቱ እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን ኢትዮጵያ በመላው ሃገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አውጃለች፡፡ ወጣቶች በጦርነቱ የተነሳ የተከሰተው የኑሮ ውድነት፣ ሰላም ማጣት፣ የሃገሪቱ እጣ ፈንታ እና የመፍተሄ አካል መሆን አለመቻል ግራ መጋባት እና ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ይናገራሉ፡፡