የነዳጅ እጥረት በአማራ ክልል

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ በመስኖ የሚያለሙ አርሶ አደሮች አሁን የተከሰተው የነዳጅ እጥረት በምርታማነታቸው ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል። በአማራ ክልል ውስጥ የበረታ የነዳጅ እጥረት ከተከሰተ ሣምንታት ማስቆጠሩ ተነግሯል። አርሶአደሮችም በተለየ ሁኔታ እንዲስተናገዱ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና የተከሰተውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ “ታይቷል” የተባለውን “ህገወጥነት” ለመቆጣጠር ዝግጅት መጀመሩን የክልሉ የንግድ ቢሮ አስታውቋል።