በፌደራል አቃቢ ሕግ ተቃውሞ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የተመስገን ደሣለኝ ምክሥሮች ቃል ሳይሰማ ቀረ፡፡
አዲስ አበባ —
በፌደራል አቃቢ ሕግ ተቃውሞ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የተመስገን ደሣለኝ ምክሥሮች ቃል ሳይሰማ ቀረ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ 6ኛ ወንጀል ችሎት ተከሣሽ ያቀረባቸውን ምሥክሮች ቃል ለመስማት ለግንቦት 22/2005 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡
ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል ባዘዘው መሠረት ምሥክሮቹ የቀረቡ ቢሆንም አቃቢ ሕግ የታዘዙለት የድምፅና የምሥል ማስረጃዎች በእጁ የገቡት “ዛሬ ስለሆነ የምሥክሮቹ ቃል መሰማት የለበትም” ሲል አቤቱታ አቅርቧል፡፡
የተከሣሽ ጠበቆች የተባለውን የድምፅና የምሥል ማስረጃ ቀደም ብለው በታዘዘው መሠረት እንዳስገቡ ገልፀው “ዘግይቷል ቢባል እንኳ የምሥክሮችን ቃል ከመስማት ሊያግድ የሚችልበት ምክንያት የለም” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
ምሥክሮቹ ተቃውሞ ባለማቅረባቸው ምክንያት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ለመስማት ቀጠሮውን መስጠቱ ታውቋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
ተመስገን ደሣለኝ - የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
Your browser doesn’t support HTML5
የተመስገን ደሣለኝ ጉዳይ ተቀጠረ