የፌደራል ማረሚያ ቤት ኃላፊዎችች ተነስተው በአዲስ ተተኩ

አዲስ አበባ የሚገኘው የፌደራል ማረሚያ ቤት

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፤ በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባሰባሰበው ሪፖርት ዘግናኝ የሆኑ ምርመራዎች የሚፈፀሙባቸው እርስ ቤቶች፤ የተዘጋውን ማዕከላዊ ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል፣ በአማራ ክልል፣ በሶማሌ፣ በደቡብ እና በሌሎች ባልታወቁ እስር ቤቶች ጭምር እንደሚፈፀሙ አስታውቋል።

የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥያቄውን ለመመለስ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አመራሮች ተነስተው በአዲስ መተካታቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ አቶ ፍሰኃ ተክሌ፤ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባሰባሰበው ሪፖርት፤ ዘግናኝ የሆኑ ምርመራዎች የተፈፀሙት በስፋት መሆኑን ፤ የሚፈፀሙባቸው እርስ ቤቶች ደግሞ የተዘጋውን ማዕከላዊ ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል፣ በአማራ ክልል፣ በሶማሌ፣ በደቡብ እና በሌሎች ባልታወቁ እስር ቤቶች ጭምር እንደሚፈፀሙ ተናግረዋል።

እነዚህን አሰቃቂ ወንጀሎች በዜጎች ላይ የፈፀሙ ሰዎች ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል፣ ተጎጂዎቹ ካሳ ሊሰጣቸውና በዘላቂነት ሊቋቋሙ ይገባል ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኃላፊዎችች ተነስተው በአዲስ ተተኩ