ፍልሰተኞች ሜድትራንያን ባህር ላይ

Your browser doesn’t support HTML5

ጣሊያንና ማልታ ወደባችን አትገቡም ማለታቸውን በመቀጠላቸው ሁለት መርከቦች ላይ ያሉ ወደአምስት መቶ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን የያዙ መርከቦች አሁንም ሜድትራንያን ባህር ላይ እየዋለሉ ናቸው። የፈረንሳዩ የህክምና ግብረ ሰናይ ድርጅት /MSF/ ድንበር የለሽ ሃኪሞች ትናንት ሰኞ ማታ ባወጣው መግለጫ፣ በአደገኛ ሁኔታ ላይ የነበሩ ተጨማሪ አንድ መቶ አምስት ፍልሰተኞችን ደርሰንላቸው /Ocean Viking/ መርከብ ላይ አሳፈረናቸዋል ብሏል።
በዚህም መርከቡ ላይ ያሉት ቁጥር ወደ 356 አድጓል። ሌሎችን አንድ መቶ ሃምሳ ፍልሰተኞች ደግሞ አሁንም ፕሮአክቲቫ ኦፕን አርምስ የተባለው የስፔይኑ ግብረ ሰናይ መርከብ ላይ ናቸው።

ቀኝ ፅንፍ የፖለቲካ አቋም አራማጁ የጣሊያን የሀገር ግዛት ሚኒስትር ማቴዎ ሳልቪኒ ሁለቱ ፍልሰተኛ ያሳፈሩ መርከቦች፣ ጣሊያን ወደብ እንዳይገቡ በፅናት መከላከሌን እቀጥላለሁ ብለዋል፡፡