የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች መሪዎች በስደተኞች ጉዳይ

Your browser doesn’t support HTML5

የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች መሪዎች በስደተኞች ጉዳይ ላይ በነገው ዕለት በኦስትሪያ ከተማ በሣልዝበርግ ሊያደርጉት የታቀደው ጉባዔ በአባል ሃገራቱ መካከል የተፈጠረው ጥልቅ መከፋፈል ሊያደናቅፈው እንደሚችል ተሰግቷል። ብራሰልስ የምትፈልገው የአውሮፓ ሕብረት የድንበር ጠባቂዎች ወደሌሎቹ ሀገሮች ዘልቀው በመግባት እንዲመደቡ ሲሆን ሌሎች እንደ ሃንጋሪ ያሉ አባል ሀገሮች ፍላጎት ግን የራሣቸውን ድንበር በራሣቸው ወታደሮች ማስጠበቅ ነው።