የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው

  • ቆንጂት ታየ

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በየመን /ፎቶ ፋይል/

ወደየመን የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁጥር ቀንሷል፡፡

የአየር ድብደባው እንደቀጠለ ነው - ሰንዓ

Your browser doesn’t support HTML5

የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው

የመን ውስጥ የተቀሰቀሰው የርስ በርስ ጦርነት በሳዑዲ አረቢያ የአየር ጥቃት ከተባባሰ ወዲህ ወደ የመን የሚገቡ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎችም ፍልሰተኞች ቁጥር ማሽቆልቆሉን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም አስታውቋል።

ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም

በመጋቢት አጋማሽ የሳዑዲ ዓረቢያ አየር ሃይል በየመን የሚደገፉት የኹጢ አማፂያን ይዞታዎችን በቦምብ መደብደብ ከመጀመሩ በፊት ባሉት ሁለት ሣምንታት ወደ የመን ይጎርፉ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ቁጥር በእጅጉ ጨምሮ እንደነበር አይኦኤም ገልጿል።

በደቡባዊቱ ግዙፍ ከተማ አደን በአየር ድብደባውና በተኩስ ልውውጡ መሃል ተጠምደናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችና ፍልሰተኛ ሠራተኞች በሚያሰሙት ተማፅኖ እንደቀጠሉ ነው፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባዎቹን የያዘውን የተያያውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡