አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ "አፋኝ" በሆኑ ሕጎች ላይ መሠረታዊ ማስተካከያ ለማድረግ እንዲሠሩ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቅርቧል፤ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አንፃር "ከፍተኛ" የተባለ የዓመት በጀት መመደቡንም አስታወቀ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
ሰማያዊ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የለውጥ ጥሪ አቀረበ
Your browser doesn’t support HTML5
የሰማያዊ ፓርቲ የዓመት በጀትና ዕቅድ
በሃገሪቱ ፓርላማ ሲፀድቁ የተቃዋሚዎችን ይሁንታ ያላገኙት አንዳንድ ሕጎች ዛሬም የልዩነት ነጥቦች ሆነው ቆይተዋል፡፡
ፀረ-ሽብር ሕጉ፣ የሲቪክ ማኅበራት ማደራጃና የመሣሰሉት ከእነዚህ ሕጎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በአብዛኛው በአንድነት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው ልዩነት በራሣቸው መንገድ መጓዝን በመረጡ አባላት በቅርቡ የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን የመሣሰሉ ሕጎች ባሉበት ሊቀጥሉ እንደማይገባ አመልክቷል፡፡
በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የሚመራው መንግሥት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አንፃር ከፍተኛ የተባለ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ለአንድ ዓመት መድቦና የሥራ ዕቅድ አዘጋጅቶ ትግሉን ለመምራት መዘጋጀቱን ፓርቲው አስታውቋል።
የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ ማሰባሰብ "በእርግጥም የሚቻል ነው" ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ለቪኦኤ ገልፀዋል።
እንዴት?
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ከቪኦኤ ጋር ተነጋግረዋል፡፡
የእስክንድር ፍሬውን ዘገባዎች ያዳምጡ፡፡