የሳዑዲ ተመላሾች ቁጥር 37 ሺህ ደረሰ፤ በናሽቪል-ቴኔሲ ሰልፍ ተደረገ

  • እስክንድር ፍሬው

የሳዑዲ ተመላሾች



Your browser doesn’t support HTML5

የሳዑዲ ተመላሾች ቁጥር 37 ሺህ ደረሰ፤ በናሽቪል-ቴኔሲ ሰልፍ ተደረገ


ሳዑዲ አረቢያ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እስካሁን 37 ሺህ የሚሆኑት አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለፀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የጠቀሱ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንዳሉት የተመላሾቱ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በይናዩትድ ስቴትስ ግዛቷ ቴኔሲ ዋና ከተማ ናሽቪል ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ትናንት ሰኞ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻቸው ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን ኢሰብአዊ ድርጊት አውግዘዋል፡፡

ሻማ በማብራትም ወገኖቻቸውን በፀሎት አስበዋል፡፡

ስብሰባውን ካስተባበሩት ኢትዮጵያዊያን መካከል አቶ መርኃ ገብረእግዚአብሔር ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።