Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት ከዋሽንግተን ዲሲው የአሜሪካ ድምጽ ዋና መሥሪያ ቤት ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
”የተዛቡ ዘገባዎችን በማሰራጨት” የከሰሱትን የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው አገልግሎት፤ የገዛ መመሪያውን ያክብር፤ ያሉት የተቃውሞ ሰልፈኞች፤ “የተዛባ አዘጋገቡንም ያቁም፤” ሲሉ፥ ጠይቀዋል።
የአሜሪካ ድምጽ በበኩሉ በቅርቡ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰልፈኞቹ ያሰሙትን ጥሪና ቅሬታ ጠቅሶ፤ አስተዳደሩ የአሜሪካ ድምጽንና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ የዜና አገልግሎቶች በሚያስተዳድረው Broadcasting Board of Governers ውስጥ የሚገኘውን ገለልተኛ ጽ/ቤት ጉዳዩን እንዲመርምር ማድረጉን አስረድቷል። የአሜሪካ ድምጽ አክሎም ጽ/ቤቱ የደረሰባቸውን ሦሥት ድምዳሜዎች ዘርዝሯል።