የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት

rally in Washington DC, August 04, 2014

«በአፍሪቃ አሕጉራዊ ልማት፥ ጸጥታ፥ ልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ፤ እንዲሁም ንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ለማጠናከር የታለመ ሳምንት፤» ዋሽንግተን “ጉባኤው ለአፍሪቃ ልማት መወጠኑ ይገባናል፤ የሕዝቡ ጉዳይ ግን የታል?” ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን የጉባኤው ተቃዋሚዎች።

Your browser doesn’t support HTML5

የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት

ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

“በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል።