የአቶ አንዳርጋቸውን መሰጠት የሚቃወሙ ሰልፎች ተደረጉ

የኢትዮጵያዊያኑ የተቃውሞ ሰልፍ የመን ኤምባሲ ደጃፍ ላይ - ዋሺንግተን ዲሲ

Your browser doesn’t support HTML5

የአቶ አንዳርጋቸውን መሰጠት የሚቃወሙ ሰልፎች ተደረጉ

የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰንዐ - የመን ላይ ተይዘው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጣታቸውን በመቃወም ዋሺንግተን ዲሲ እና በአባባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የመን ሪፐብሊክ ኤምባሲ ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል፡፡

የመን ኤምባሲ ደጃፍ ላይ የተገኙት ኢትዮጵያዊያን የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷ ያስቆጣቸው መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ከኤምባሲው የሚወጡና የሚገቡ ተሽከርካሪዎችና ሠራተኞችን በብዙ ድምፅ፣ ጩኸትና መፈክር አውከዋል፡፡ የመን ሽብርተኛ፣ ሃፍረት ለእናንተ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ የየመንን ባንዲራና የፕሬዚዳንቷን ፎቶ አቃጥለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡