የመን ውስጥ ስላሉ ኢትዮጵያዊያን

  • ቆንጂት ታየ

ያሪም ከተማ - ኢብ ክፍለሃገር ከሳዑዲ መሩ የአየር ድብደባ በኋላ

ፓኪስታንና ሌሎች ሃገሮች ዜጎቻቸውን ከየመን እያስወጡ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

የመን ውስጥ ስላሉ ኢትዮጵያዊያን

በየመን በሺአ ሁጢ አማፂያንና በሀገሪቱ ፕሬዚደንት ታማኝ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው።

በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ኅብረት ጄቶች በሺአ ሁጢ ሸማቂዎቹ ይዞታዎች ላይ ላለፉት ሁለት ሣምንታት ድብደባ ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

በዚያች ድሃ ሃገር ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም ኣሳሳቢ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች ሲያስገነዝቡ ቆይተዋል።

የመን ውስጥ በሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንዲሁም የሥራ ፍልሰተኞች አሉ።

“ከተማይቱ በአሥሮፕላን እየተደበበደበች ነው፤ ካለንበት እየሸሸን ነው፤ የሽሽት ነገር ሆኖ ነው እንጂ እዚህ ቦታ ብንሄድ እንተርፋለን ብለን አይደለም፤ ወዳገኘነው አቅጣጫ ነው የምንሄደው፤ ወደ ሦስት መቶ እንሆናለን” ብለዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።