“በተለያዩ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች በቤት ሰራተኝነት የሚሄዱ ኢትዮጲያውያት የሚደርስባቸው ስቃይ” ጥናታዊ ገለጻ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት

  • konjit taye

“በተለያዩ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች በቤት ሰራተኝነት የሚሄዱ ኢትዮጲያውያት የሚደርስባቸው ስቃይ” በቅርቡ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በተካሄደ ዝግጅት ላይ ጥናታዊ ገለጻ ካደረጉት ተካፋዮች መካከል አንዲቱ የሆነችው ወይዘሪት ሰላማዊት ተስፋዬ ያተኮረችበት ርዕስ ነበር።

በዋሽንግተን የሚገኘው የጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ የህግ ማዕከል በሚያካሂደው Leadership and Advocacy for Women in Africa ወይም LAWA በተሰኘው መርሃ ግብር ውስጥ የህግ ትምህርቱዋን በመከታተል ላይ ያለችው ወይዘሪት ሰላማዊት ማዕከሉ ባዘጋጀው ምክር ቤታዊ ገለጻ ላይ በርዕሱ ዙሪያ ያካሄደችውን ጥናት በተመረኮዘው ገለጻዋ ችግሩን ለመቅረፍ ይበጃሉ ያለቻቸውን የመፍትሄ ሃሳቦችም ጠቁማለች።

ለሴቶችና ቤተሰብ ፕሮግራም ከሰጠቸው ቃለ መጠይቅ የዛሬውን ሁለተኛና የመጨረሻ ክፍል ያድምጡ።