በለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በቂሊንጦ እስረኞች አሟሟት ጥያቄ አቀረቡ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ፋይል- ለንደን ከተማ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሞቱ እሥረኞች አስከሬን ምርመራ ተደርጎበት ያሟሟታቸው ሁኔታ እንዲጣራና ውጤቱ ለሕዝብ በአስቸኳይ እንዲገለጽ በለንደን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ጠዋት በዚያ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገለጹ።

እነዚሁ 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እስከ ኤምባሲው ቢሮዎች ዘልቀው በመግባት ለ45 ደቂቃዎች ያህል ጽሕፈት ቤቱን ተቆጣጥረው እንደነበርና፥ በውስጡ ያገኙትን ሰንደቅ ዓላማ አንስተው ይዘው በገቡት ባለ አረንጓዴ፥ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ ዓላማ መተካታቸውንም ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕዝብ ለቀረቡ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እየሰጠ ነው፣ የኤምባሲውን የዕለት ተለት ተግባር ለማደናቀፍ በሃይል ገብተው ግርግር ለፈጠሩ ሕገወጦች ግን መልስ አልሰጥም። ጉዳዩ በሕግ ተይዟል” ሲሉ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የኤምባሲው ሠራተኛ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በቂሊንጦ እስረኖች አሟሟት ጥያቄ አቀረቡ