በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሞኑ እንቅስቃሴ ወቅት ፈጽሟል ያሏቸውን የመብት ጥሰቶች በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
ዋሽንግተን —
የተቃውሞ ሰልፎቹ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ባለፈው ሳምንት፣ ለንደን በትናንቱ ዕለት፣ ዛሬ ደግሞ በቺካጎና በጄኔቫ ተካሂደዋል።
በለንደን ሰልፈኞቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈጸማል ያለቱን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ በመቃወም የተካሄደው ትዕይንተ-ሕዝብ ሰላማዊና በጥሩ መንፈስ የተካሄደ፣ ኃላፊነትም በተሞላበት ሁኔታ መከናወኑን አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መፈክሮች መካከልም፣ የእንግሊዝ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቁም፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ ጋዜጠኞችን ማዋከብና ማሰር ይቁም፣ ወዘተ የሚሉ ይገኙባቸዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5