ኢትዮጵያውያን-በአሜሪካ

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴይትስ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው፣ ስራ ለማግኘትና በዘርፉም የንግድ ተቋማት እስከማቋቋም ደርሰዋል። ብዙዎቹ በዘርፉ የተሰማሩት ኢትዮጵያ በነበሩባቸው ጊዚያት የወሰዷቸው ስልጠናና የስራ ልምዳቸው ከዘርፉ ጋር የተገናኘ ቢሆንም፤ አንዳንዶች ደግሞ ፍጹም የተለየ የሙያ ስልጠና ወስደው ከጥብቅና፣ ከትወና፣ ከማምህርነት ወደ IT(የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ) ስራቸውን ያዞሩም በርካታ ናቸው።