የአፍሪካ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ሁለት ኢትዮጵያዊ ፊልሞች ተወዳድረው አድናቆትን አተረፉ

Your browser doesn’t support HTML5

ባሳለፍነው ወር መጨረሻ በዛንዚባር በተዘጋጀው ዚፍ /ZIff/ በተሰኘው የአፍሪካ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ሁለት ኢትዮጵያዊ ፊልሞች ለውድድር ቀርበው ነበር። በአጭር የፊልም ዘርፍ የማንተጋፍቶት ስለሺ "ግርታ" እና በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ የተሰራውና በሰሎሜ ሙሉጌታ የተዘጋጀው "ዉቭን" በአማርኛው የተሸመነ የተሰኘው ወጥ ሙሉ ፊልም ከሌሎች የአፍሪካ ፊልሞች ጋር በዘርፉ ባለሙያዎች ለመታየት በቅቷል። ከአጭር የፊልም ዘርፍም "ግርታ" ተሸላሚ ሆኗል። አዘጋጆቹን አነጋግረናል።