የዓለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ያገለገሉት ማርጋሪት ቻን ሥልጣን ሊለቁ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

የሥራ ዘመናቸውን አጠናቀው ሥልጣን የሚለቁት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ማርጋሪት ቻን፣ የዘንድሮውን የድርጅቱን ጉባዔ የከፈቱት አሁን አሁን ድርጅቱ፣ ዋጋውን እያጣ ነው የሚሉትን ሰዎች ትችት ጠንከር ባላ ኃይለ ቃል በማስተባበል ነው፡፡ ማርግሪት ቻን ለአለፉት አሥር ዓመታት የዓለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ካገለገሉ በኋላ ሥልጣን ሊለቁ ሲሆን ነገ ማክሰኞ ለሚመረጥ ይህን ለዓለም ጤና ጥበቃ ዋና ቁልፍ የሆኑ ድርጅት ለሚመራ ሰው ሥልጣኑን ሊያስረክቡ ነው፡፡